"በትምህርት ቤቶች ስፓርት ሊግ ውድድርን ባህል በማድረግ ጤናማ ፣ ንቁና ብቁ ትውልድ እንፈጥራለን !" በሚል መሪ ቃል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተለያዩ የስፓርት ዓይነቶች በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የስፖርት ውድድር የፊታውራራ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክፍለ ከተማ ውስጥ ባሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በሴቶች እግር ኳስ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል። ት/ቤታችንን በመወከል
በአትሌትክስ ዘርፍ በ5000ሜትር የሴቶች ሩጫ ተማሪ ጂቱ ሞቱማ 1ኛ በመውጣት ስታሸንፍ ተማሪ አብሳላት ዴቼሎ 2ኛ ወጥታለች። በወንዶች 5000ሜትር ተማሪ ሚኪያስ ለማ 3ኛ፤ ተማሪ ፋኖስ ያደቻ 1500ሜ 1ኛ ፣ተማሪ አዲሱ ደጀኔ 1500ሜ 3ኛ፣ተማሪ ሀና ትልቁ በ800ሜ 2ኛ፣ ተማሪ ሀሰን ኑርሁሴን እና ተማሪ ራኦል አይቸው በ100ሜ ሩጫ 2ኛ ና 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነው ክፍለ ከተማችንን ወክሎ በከተማ ደረጃ ለሚደረገው ውድድር ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ። እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን!!!
.